Artificial intelligence

✴️ የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገፅ ልጥፎቻችን ስለ አዕምሮ ጤናችን ምን ይናገራሉ?

🏳️ የአሜሪካው ዳርትማውዝ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ሬዲት በተባለው የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገፅ የሚለጠፉ አስተያየቶችን መሠረት አድርጎ የሰዎችን የአዕምሮ ጤናማነት የሚለይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ማበልፀጋቸው ተነገረ፡፡

🏳️ የተመራማሪዎቹ ትኩረት እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና ሌሎች የስሜት ቀውሶች ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለምርምሩ የሚሆን ዳታ የስሜት ቀውሶቹ ተጠቂ መሆናቸውን ካመኑ እና ምንም አይነት የሚታወቅ የአዕምሮ እክል ከሌለባቸው ሰዎች ተሰብስቧል፡፡

🏳️ ይህ ዳታ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱን ለማሰልጠን ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በውጤቱም ይዘቶቹ “ደስታ” “ንዴት” “ሐዘን” “ፍርሐት” “ስሜት አልባ” ወይም ድብልቅ ስሜቶችን ያንጸባርቃሉ የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ እንደሚቻል ተመላክቷል፡፡

🏳️ ሥርዓቱ ከልጥፉ ይዘት ባሻገር ስሜት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ቴክኤክስፕሎር አስነብቧል፡፡

🏳️ ሰዎች በፈቃደኝነት የሚለጥፏቸውን ይዘቶች መሠረት አድርጎ በቀላሉ ባሕርያቸውን ለመረዳት የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገጾች ጥሩ አማራጭ መሆናቸውን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

🏳️ ምርምሩ የአዕምሮ የጤና እክልን ስር ሳይሰድ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ የምሁራኑ እምነት ነው፡፡
©EAII
════❁✿❁ ═══════ 🎮▩♦️. @ELA_TECH
🎯▩♦️. @ELA_TECH_GROUP
🚀▩♦️. @ELA_TECHBOT

Leave a Reply

Create your own website, free on WordPress.com.Create your own website.
Start free